am_tn/isa/62/03.md

1.3 KiB

በያህዌ እጅ የውበት አክሊል በአምላክሽ እጅ እንደ ነገሥታት ዘውድ ትሆኛለሽ

ሁለቱም ተመሳሳይ ነገር ማለት ሲሆኑ፣ ተያይዘው የቀረቡት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ኀይልና ሥልጣን ሥር ኢየሩሳሌም የንጉሥ ከተማ እንደምትሆን ይናገራሉ፡፡ የያህዌ እጅ የእርሱን ኀይልና ሥልጣን ይወክላል፡፡

ከእንግዲህ… ‹‹የተተወች››… አትባዪም

ሁለቱም ተመሳሳይ ነገር ማለት ሲሆኑ፣ ተያይዘው ያቀረቡት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

ከእንግዲህ ስለ አንቺ አይባልም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች አንቺን አይሉሽም››

ከእንግዲህ ስለ ምድርሽ አይባልም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ሰዎች ስለ ምድርሽ አይሉም››

ምድርሽ ታገባለች

ይህ ማለት ያህዌ የእስራኤልን ሕዝብ ይወዳል፤ እንደ ባል ሁሌም ከእነርሱ ጋር ይሆናል ማለት ነው፡፡