am_tn/isa/62/01.md

852 B

ስለ ጽዮን ዝም አልልም፤ ስለ ኢየሩሳሌም ጸጥ አልልም

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ እዚህ ላይ፣ ‹‹ጽዮን›› እና፣ ‹‹ኢየሩሳሌም›› በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ኢየሩሳሌም ሕዝብ ዝም አልልም››

ዝም አልልም

‹‹እኔ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡

ጽድቋ ደምቆ እስኪወጣ፣ ድነቷ እንደ ፋና እስኪሆን ድረስ

ሁለቱም ሐረጐች የሚያመለክቱት የኃላ ኀላ እግዚአብሔር መጥቶ የእስራኤልን ሕዝብ እንደሚያድን ያም የብርሃን ያህል በግልጽ እንደሚታይ ነው፡፡