am_tn/isa/61/01.md

797 B

የያህዌ መንፈስ እኔ ላይ ነው

እዚህ ላይ፣ ‹‹መንፈስ›› ሰዎችን የሚያነሣሣና የሚያንቀሳቅስ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ኢሳይያስ 11፥2 ወይም ኢሳይያስ 42፥1 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ለተጐዱ

ይህ ታላቅ መከራ ውስጥ ያሉ ድኾችን ወይም፣ በራሳቸው ማስወገድ የማይችሉት ችግር ውስጥ ያሉ ጭቁኖችን ያመለክታል፡፡

ለምርኮኞች ነጻነት፣ ለእስረኞች መፈታት

ሁለቱም ሐረጐች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለምርኮኞች ነጻነትን በእርግጥ እንደሚሰጥ ያመለክታሉ፡፡