am_tn/isa/59/17.md

783 B

ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤ የድነትን ቁር ራሱ ላይ ደፋ፡፡ በቀልን ለበሰ፤ ቅናትን እንደ መጐናጸፊያ ደረበ

‹‹ጥሩር››፣ ‹‹ቁር››፣ ‹‹ልብስ›› እና፣ ‹‹መጐናጸፊያ›› በጦርነትና በውጊያ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡ ሕዝቡን ለመቅጣት ያህዌ እነዚህን እንደ ለበሰ ኢሳይያስ ይናገራል፡፡

መጐናጸፊያ

ከላይ እስከ ታች የሚዘልቅ ሰፊ ልብስ

ከፈላቸው

ኢሳይያስ ወደ ፊት የሚሆኑ ነገሮች ባለፈው ጊዜ እንደሆኑ አድርጐ ይናገራል፡፡ ይህም በእርግጥ ይፈጸማል ማለት ነው፡፡