am_tn/isa/59/16.md

987 B

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ መናገር ቀጥሏል፡፡

ሰው እንደሌለ አየ፤ ጣልቃ የሚገባ ባለ መኖሩ ተገረመ

‹‹መከራ ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ማንም ባለ መምጣቱ ያህዌ ተገረመ›› ወይም፣ ‹‹መከራ ውስጥ ያሉትን ለመርዳት የመጣ ሰው ባለመኖሩ ያህዌ ተደነቀ››

ስለዚህ የገዛ ራሱ ክንድ ማዳን አመጣለት

የያህዌ፣ ‹‹ክንድ›› ችሎታውንና ኀይሉን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝቡን ለማዳን ያህዌ የራሱን ኀይል ተጠቀመ››

ጻድቁ ደግፎ ያዘው

እዚህ ላይ፣ ‹‹ጽድቅ›› የሰው ባሕርይ እንዳለው ተነግሯል፡፡ ይህን ቃል ቅጽል ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁሌም እንደሚያደርገው መልካም አደረገ››