am_tn/isa/59/03.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

እጃችሁ በደም፣ ጣቶቻችሁም በኀጢአት ቆሽሸዋል

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› እና፣ ‹‹ጣቶች›› ድርጊታቸውን ያመለክታሉ፡፡ ይህም ማለት ግፍና ኀጢአት በመፈጸም በድለዋል ማለት ነው፡፡ ‹‹የእናንተ›› ብዙ ቁጥር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከባድ ኀጢአቶች ፈጽማችኃል››

ከንፈሮቻችሁ ሐሰት ተናገሩ፣ ምላሶቻችሁ ሐሜት ተናገሩ

ሰዎች እንዲናገሩ የሚረዱ የአካል ክፍሎች ንግግርን ይወክላሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሐሰትና ሐሜት ትናገራላችሁ››

ችግር ፀነሱ፤ ኀጢአትን ወለዱ

‹‹መፅነስ›› እና ‹‹መውለድ›› ምን ያህል ተዘጋጅተው ኀጢአት እንደሚያደርጉ ያመለክታል፡፡ ‹‹እነርሱ›› የሚለው የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀጢአት ለማድረግ በርትተው ይሠራሉ››