am_tn/isa/58/08.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ያኔ ብርሃንህ እንደ ንጋት ጮራ ይፈነጥቃል

‹‹ይፈነጥቃል›› ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን፣ ደምቆ ያበራል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ችግረኞችን ቢረዱ ከጨለማው ሌሊት በኃላ እንደሚመጣ ፀሐይ ተግባራቸው ሌሎች ሰዎች የሚያዩት ብርሃን ይሆናል ማለት ነው፡፡ ወይም ብርሃን እነርሱ ላይ የሚያበራውንና የሚባርካቸውን የጌታ ብርሃን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡

ፈውስህ ፈጥኖ ይበቅላል

ይህ ማለት ቶሎ እንደሚድን ቁስል እግዚአብሔር ቶሎ ይባርካቸዋል ይመልሳቸዋል ማለት ነው፡፡

ጽድቅህ በፊትህ ይሄዳል፤ የያህዌ ክብር ደጀን ይሆንልሃል

ይህ ከግብፅ በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ጥበቃ ያመለክታል፡፡ ይህ መልካም የሆነውን ቢያደርጉ እግዚአብሔር እንደ ገና ከጠላቶቻቸው ይጠብቃቸዋል ማለት ነው፡፡

ጽድቅህ

ይህ አገላለጽ በዕብራይስጥ ጽድቅን እንዲያውም ድልን የሚሰጥ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል፡፡ በዚህ ዐውድ የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡ ጥቂት የዘመኑ ቅጂዎች ይህን ትርጒም ይዘዋል፡፡