am_tn/isa/58/04.md

1.5 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ለጥያቄያቸው መልስ በመስጠት ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

እነሆ

‹‹ተመልከቱ›› ወይም፣ ‹‹ልብ በሉ›› ልብ እንዲሉ በመናገር ያህዌ ለጥያቄያቸው መልስ ይሰጣል፡፡

የግፍ ጡጫ

‹‹የግፍ ጡጫ›› — ይህ የምር መደባደባቸውን ያመለክታል፡፡ ‹‹ጡጫ›› በግልጽ የሚታይ ቁጣን ያመለክታል፡፡

እኔ የምፈልገው ጾም ይህን ነውን… ራሱን የሚያዋርደው?

ሕዝቡን ለመገሠጽ ያህዌ ጥያቄ ያነሣል፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን እንዳዋረዱ ያስመስላሉ፤ ግን ሰዎችን ይጐዳሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለም… ራሱን እንዲያዋርድ››

ሰው ራሱን የሚያዋርደው እንደ ደንገል ራሱን ዝቅ የሚያደርገው

ይህ ሰውየው ዝቅ ብሏል፤ ግን በእውነት ትሑት አይደለም ማለት ነው፡፡ ‹‹ደንገል›› በቀላሉ የሚታጠፍ ደካማ ተክል ይወክላል፡፡

ይህን ጾም ትለዋለህ፤ ያህዌን ደስ የሚያሰኝ ቀን ትለዋለህ?

ያህዌ ጥያቄ ያቀረበው ሕዝቡን ለመገሠጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መቼም እንዲህ ያለውን ጾም እኔን ያስደስታል ብለህ አታስብም!