am_tn/isa/57/14.md

1.4 KiB

አብጁ አብጁ! ከሕዝቤ መንገድ እንቅፋት አስወግዱ

ሕዝቡ ወደ እርሱ እንዲመለሱና እርሱን ለማምለክ እንቅፋቶች እንዳይኖሩ ያህዌ አጽንዖት በመስጠት መንገዱ በአስቸኳይ እንዲስተካከል ይናገራል፡፡ ይህ ኢሳይያስ 40፥3 ላይ ያለውን ያስተጋባል፡፡

ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው ይህን ይናገራል

‹‹ከፍ ያለ›› እና፣ ‹‹ልዕልና›› በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ያላቸው ቢሆኑም፣ ያህዌ ከፍ ያለ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ ኢሳይያስ 6፥1 እና 33፥10 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ ኢሳይያስ 52፥13 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

የትሑንን መንፈስ ለማነሣሣት፣ የልበ ሰባራዎችን ልብ ለማነሣሣት

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ቢሆኑም፣ በፊቱ ትሑት የሆኑትን እንደሚያበረታና እንደሚያጽናና አጽንዖት ይሰጣል፡፡

መንፈስ… ልብ

እነዚህ የሰውን ሐሳብና ስሜት ያመለክታሉ፤ ቃል በቃል መንፈስና ልብ ማለት አይደለም፡፡