am_tn/isa/57/13.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእምነተ ቢሶቹ የእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

የጣዖቶችሽ ብዛት ያድኑሽ

ያህዌ በሕዝቡና በጣዖቶቻቸው እያፌዘ ነው፡፡ ምንም እንኳ እንደማያድኑዋቸው ቢያውቅም ያህዌ ጣዖቶቹ ሕዝቡን እንዲያድኑ ይናገራል፡፡

ሁሉንም ነፋስ ይወስዳቸዋል፤ እስትንፋስ ሁሉንም ይጠራርጋቸዋል፡፡

ጣዖቶቹ ዐቅመ ቢስና ከንቱ መሆቸውን አጽንዖት ለመስጠት በሁለት መንገዶች ተመሳሳይ ነገር ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ነፋስ ወይም እስትንፋስ እንኳ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል››

የተቀደሰ ተራራ

‹‹የተቀደሰ ተራራ›› በኢየሩሳሌም ያለው የጽዮን ተራራ ነው፡፡ ኢሳይያስ 11፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡