am_tn/isa/57/11.md

954 B

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእምነተ ቢሶቹ የእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

እኔን የዋሸሸኝ ማንን ፈርተሸ፣ ማንንስ ሠግተሸ ነው?

ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው ሕዝቡን ለመገሠጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔን ለመዋሸት እነዚህን ጣዖቶች በእርግጥ መፍራት አለብሽ››

እኔን አላስታወስሽም፤ ስለ እኔ አላሰብሽም

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ሲሆኑ፣ ሕዝቡ ያህዌን ማስታወስ ቢኖርባቸውም እነርሱ እንደዚያ እንዳላደረጉ አጽንዖት ይሰጣል፡፡

ጽድቅሽንና ሥራሽንም ሁሉ እገልጣለሁ

እዚህ ላይ ክፉ ሥራቸውን ጽድቅ ብሎ በመጥራት ያህዌ በስላቅ እየተናገረ ነው፡፡