am_tn/isa/56/09.md

1.0 KiB

እናንት የምድር አራዊት ሁሉ እናንት የዱር አራዊት ሁሉ መጥታችሁ በጫጭቁ

በዱር አራዊት የሚመስላቸውን የሌላ አገር ሰራዊት መጥተው የእስራኤልን ሕዝብ እንዲያጠቁ እግዚአብሔር ይጠራል፡፡

ጠባቂዎቻቸው ሁሉ ዕውሮች ናቸው

ይህ ማለት የእስራኤል መሪዎች ማኅበረ ሰቡ ውስጥ እየሆነ ያለውን ማየት አልቻሉም ምናልባትም አልፈለጉም ማለት ነው፡፡

ሁሌም ዝም ያሉ ውሾች ናቸው

መሪዎቹ ሕዝቡን ማስጠንቀቅ ነበረባቸው፣ ግን ያን አላደረጉም፡፡ ማኀበረ ሰቡ ውስጥ አንድን ሰው በውሻ መመሰል ትልቅ ስድብ ነው፡፡

ተጋድመው ያልማሉ፤ መተኛት ይወዳሉ

ይህ ማለት መሪዎቹ የእግዚአብሔርን ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ አያመጡም፤ ግን የራሳቸውን ምቾት ብቻ ይፈልጋሉ ማለት ነው፡፡