am_tn/isa/55/12.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

በሰላም ትመራላችሁ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሰላም እመራችኃለሁ››

ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤ የሜዳ ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ

ተራሮችና ኮረብቶች ድምፅና እጆች እንዳሉዋቸው ሰዎች ያህዌ ሕዝቡን ሲታደግ ደስ እንደሚላቸው ያህዌ ይናገራል፡፡

በእሾኽ ፈንታ የጥድ ዛፍ፣ በኩርንችት ፈንታ ባርሰነት ይበቅላል

‹‹እሾኽ›› እና ‹‹ኩርንችት›› የሚዋጋ እሾኽ ያላቸው ተክሎችን ያመለክታሉ፡፡ ‹‹የጥድ ዛፍ›› እና፣ ‹‹ባርሰነት›› ሁሌም ለምለም የሆኑ ዛፎችን ያመለክታሉ፡፡ እሾኻማ ተክሎች ጥፋትን ሲወክሉ፣ ለምለም ዛፎች ግን ሕይወትንና ብልጽግናን ይወክላሉ፡፡

ለስሙ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ስም›› የያህዌን ዝና ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእርሱ ዝና›› ወይም፣ ‹‹ለእርሱ ክብር››

አይቆረጥም

መኖሩን የሚያቋርጥ ነገር ከዛፍ እንደ ተቆረጠ ቅርንጫፍ ወይም ከልብሱ እንደ ተቀደደ ቅዳጅ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አያልቅም›› ወይም፣ ‹‹ለዘላለም ይኖራል››