am_tn/isa/55/10.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ዝናብና በረዶ… እንደማይመለስ

ይህ የሚያመለክተው ዝናብና በረዶ እንደሚተንን ነው፡፡

እንዲሁ ቃሌ… እኔ የላክሁትን ዓላማ ይፈጽማል

ቃሉ አንድ ነገር እንዲያደርግ እንደ ተላከ መልእክተኛ እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡

ከአፌ የወጣ ቃሌ

እዚህ ላይ፣ ‹‹አፍ›› ያህዌ ራሱን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ የምናገረው ቃል››

ወደ እኔ ባዶውን አይመለስም

እዚህ ላይ ቃሉ ወደ ያህዌ መመለሱ እርሱ የላከውን ሥራ ማከናወኑን ያመለክታል፡፡ ‹‹ባዶውን›› አይመለስም ማለት ሥራውን ሳይፈጽም አይቀርም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሥራውን መፈጸሙ አይቀርም››