am_tn/isa/55/02.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ትመዝንላችሁ… በማያጠግብስ… ለምን ጉልበታችሁን ትጨርሳላችሁ?

ያህዌ ጥያቄዎቹን ያቀረበው ሕዝቡን ለመገሠጽ ነው፡፡ ከያህዌ ውጪ ደስታ ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች መብል ላልሆነ ነገር ገንዘብ ከማውጣትና ለማያጠግብ ነገር ጉልበትን ከመጨረስ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብ ማውጣት የለባችሁም… ለማያጠግብ ነገር መሥራት የለባችሁም››

ብራችሁን ለምን ትመዝናላችሁ

ይህ የሚያመለክተው ለአንዳች ነገር ለመክፈል የብር ሳንቲሞችን መቁጠርን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ገንዘብ መክፈል››

እንጀራ ላልሆነ ነገር

እዚህ ላይ፣ ‹‹እንጀራ›› በአጠቃላይ ምግብን ይወክላል፡፡ ሰዎቹ ገንዘብ ያወጡ የነበረው ምግብ ላልሆነ ነገር ነበር፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምግብ ላልሆኑ ነገሮች››

መልካም የሆነውን ብሉ፣ በጮማ ደስ ይበላችሁ

በያህዌ በረከትና ደስታ የሚተማመኑ ሰዎች ደስ የሚያሰኛቸውን መልካም ምግብ እንደሚበሉ ሰዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በጮማ

‹‹ጮማ›› ውስጡ ብዙ ስብ ያለው ሥጋ ሲሆን፣ መልካም ምግብን የሚወክል ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምርጥ በሆነ ምግብ››