am_tn/isa/55/01.md

846 B

በኢሳይያስ በኩል ያህዌ በምርኮ ላሉ የኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡ አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ የሚበላና የሚጠጣ ነገር በነጻ እንደሚሰጥ፣ እርሱም ሕዝቡን በነጻ እንደሚባርክ ይናገራል፡፡

ኑ… ኑ

ይህ ቃል መደገሙ የግብዣውን አጣዳፊነት ያመለክታል፡፡

ወይን ጠጅና ወተት ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ ግዙ

ብዙውን ጊዜ አንዳች ነገር ለመግዛት ማንም ገንዘብ መክፈል ያለበት እንደ መሆኑ መጠን፣ ይህ ዐረፍተ ነገር ስላቅ ይመስላል፡፡ ይህ አጽንዖት የሚሰጠው እነዚህን ነገሮች በነጻ ለመስጠት የያህዌን አስደናቂ ጸጋ ነው፡፡