am_tn/isa/54/17.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ይከሽፋል

የጠላት ሐሳብ በያህዌ ሕዝብ ላይ አለመሳካቱ፣ እነርሱ ላይ የተሠራ መሣሪያ መክሸፍ ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶች አንቺ ላይ መሣሪያ ያበጁ ይሆናል፤ ግን አያሸንፉሽም››

የያህዌ ባርያዎች ርስት ይህ ነው

ለሚያገለግሉት ሰዎች ያህዌ የሚሰጠው ሽልማት ርስታቸው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይላል ያህዌ

የተናገረው እርግጥ መሆኑን ለማሳየት ያህዌ ስሙን በመጥራት ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ኢሳይያስ 30፥1 ላይ ያለውን እንደ ተረጐምህ ተርጉመው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የተናገረው ይህን ነው›› ወይም፣ ‹‹እኔ ያህዌ የተናገርሁት ይህን ነው››