am_tn/isa/54/11.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

የተጨነቅሽ

እዚሀ ላይ ያህዌ የምትሰማው ይመስል ለኢየሩሳሌም ይናገራል፡፡ ኢየሩሳሌም እዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ትወክላለች፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናንት የተጨነቃችሁ የኢየሩሳሌም ሰዎች››

በዐውሎ ነፋስ የተወሰድሽ

ሕዝቡ በዐውሎ ነፋስና በማዕበል ተወስደውና ተጐድተው እንደ ነበር ያህዌ ይናገራል፡፡ ይህም በጣም የተጐዱና መረጋጋትም እንዳልነበራቸው ያመለክታል፡፡

ያልተጽናናሽ

‹‹አጽናኝ የሌለሽ››

በሰንፔር ድንጋይ እመሠርትሻለሁ… በከበሩ ድንጋዮች አስጌጥሻለሁ

ያህዌ ኢየሩሳሌምን እንደሚመሠርትና ውብ እንደሚያደርጋት ባማሩ ቃላት ይናገራል፡፡ ምንም እንኳ የተጋነነ ቢመስልም ያህዌ በተናገረው መሠረት መተርጐም አለበት፡፡

የሚያብረቀርቅ ዕንቁ… ሰንፔር… ቀይ ዕንቁ

እነዚህ ሁሉ የከበሩ ድንጋዮች ናቸው፡፡ የሚያብረቀርቅ ዕንቁ ነጣ ያለ ሰማያዊና አረንጋዴ ነው፤ ሰንፔር ጥቁር ሰማያዊ ነው፤ ቀይ ዕንቁ ቀይ ሐምራዊ ነው፡፡