am_tn/isa/54/09.md

1.7 KiB

የኖኅ ውሆች

ይህ በኖኅ ዘመን ያህዌ ያደረገውን ጐርፍ ያመለክታል፡፡

ተራሮች ቢወድቁና ኮረብቶችም ቢናወጡ እኔ ለአንቺ ያለኝ ፍቅር

እነዚህ መስፈርቶች ቢሟሉ ኖሮ ምን ይሆን እንደ ነበር ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተራሮች ቢወድቁ፣ ኮረብቶችም ቢናወጡ ለአንቺ ያለኝ ፍቅር››

ኮረብቶችም ቢናወጡ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ኮረብቶች ይናወጡ ይሆናል››

ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ግን ከአንቺ አይመለስም

ያህዌ ለሕዝቡ ያለው ቀጣይ ፍቅር፣ ከሕዝቡ በማይመለስ ነገር ተመስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንቺን መውደዴን አልተውም››

የሰላሜም ኪዳን አይናወጥም

ያህዌ ከሕዝቡ ጋር ያለውን ኪዳን አለመሻሩ፣ ኪዳኑ የማይናወጥ ነገር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሰላም ኪዳኔን አልሽርም›› ወይም፣ ‹‹በኪዳኔ በሰጠሁሽ ተስፋ መሠረት ሰላሜን በእርግጥ እሰጥሻለሁ››

የሚራራልሽ ያህዌ እንዲህ ይላል

እዚህ ላይ ያህዌ ስለ ራሱ በሦስተኛ ሰው ደረጃ ይናገራል፡፡ በመጀመሪያ ሰው መግለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምራራልሽ እኔ ያህዌ የምለው ይህን ነው››