am_tn/isa/54/02.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ድንኳንሽን አስፊ… ካስማሽንም አጠንክሪ

ይህ ኢሳይያስ 54፥1 ላይ የጀመረው ምሳሌ ቀጣይ ነው፡፡ ሕዝባቸው እጅግ ስለሚበዛ እንዲዘጋጁ ያህዌ ለኢየሩሳሌም ሰዎች ይናገራል፤ የሕዝባቸው መብዛት ለብዙ ልጆች የሚበቃ ክፍል እንዲኖር ድንኳንዋን እንድታሰፋ ይናገራል፡፡

ትስፋፊያለሽ

እዚህ ላይ፣ ‹‹አንቺ›› ነጠላ ቁጥር ሲሆን፣ መካን ስለሆነች ሴት ያመለክታል፡፡ እርሷ የሚለው ራስዋንና ዘሮችዋን ሁሉ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንቺና ዘሮችሽ ትስፋፋላችሁ››

ሕዝቦችን ያሸንፉሉ

‹‹ሕዝቦች›› ሰዎችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሌላ አገር ሕዝቦችን ያሸንፋሉ››