am_tn/isa/54/01.md

1.0 KiB

አንቺ መካን ሴት… ያላገባች ሴት ልጆች

እንደ ገና በኢየሩሳሌም ብዙ ሰዎች ስለሚኖሩ ደስ እንዲላቸው ያህዌ ለሕዝቡ ይናገራል፡፡ ይህንን በተመለከተ ያላገባች ሴት ብዙ ልጆች ይኖሩዋታል ማለት መሆኑን ያህዌ ይናገራል፡፡

አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ ዘምሪ፣ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ

ይህ ከመጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

የተተወችው ሴት ልጆች በዝተዋልና

ወደ ፊት የሚሆነው ነገር ባለፈው ጊዜ እንደ ተፈጸመ ተደርጐ ተነግሯል፡፡ ይህም ነገሩ በእርግጥ እንደሚሆን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የተተወችው ሴት ልጆች እጅግ ብዙ ይሆናሉ››

የተተወችው

እዚህ ላይ፣ ‹‹የተተወችው›› ማለት ባልዋ የናቃትና የተዋት ሴት ማለት ነው፡፡