am_tn/isa/53/08.md

1.9 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ያህዌ ባርያ መናገር ቀጥሏል (ኢሳይያስ 53፥1-2 ይመ.)

በማስጨነቅና በፍርድ ተወገዘ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ ‹‹ማስጨነቅ›› የሚለውን አንዳንድ ቅጂዎች ‹‹በእስራት›› ብለውታል፡፡ እንደ እነዚህ ቅጂዎች ከሆነ፣ የያህዌ ባርያ ይታሠራል፣ ከዚያም ይፈረድበታል፣ ይወገዛል ማለት ነው፡፡

ከዚያ ትውልድ ስለ እርሱ የሚያስብ ማን ነው?

ጥያቄው አጽንዖት የሚሰጠው ስለ እርሱ የሚያስብ አለመኖሩን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእርሱ ትውልድ እርሱ ላይ ለሆነው የሚያስብ የለም›› ወይም፣ ‹‹በዘመኑ ከነበሩ ሰዎች መካከል እርሱ ላይ ስለ ሆነው የሚያስብ የለም፡፡››

ከዚያ ትውልድ ስለ እርሱ የሚያስብ ማን ነው?

ይህን የዕብራይስጥ ምንባብ ብዙ ቅጂዎች በተለያየ መንገድ ተርጉመውታል፡፡ ‹‹ስለ ዘሮች የሚናገር ማን ነው? ወይም፣ ‹‹ስለ ዕጣ ፈንታው የሚናገር ማን ነው?

እርሱ ግን ከሕያዋን ምድር ተቆረጠ

‹‹መቆረጥ›› መሞት ማለት ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ግን ሞተ›› ወይም፣ ‹‹ግን ሞት ወሰደው››

ስለ ሕዝቤ

‹‹ስለ እስራኤል ሕዝብ››

በአፉ ምንም ተንኰል አልተገኘም

‹‹አፍ›› ሰው የሚናገረውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በንግግሩ ማንንም አላታለለም››