am_tn/isa/53/07.md

1008 B

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ያህዌ ባርያ መናገር ቀጥሏል (ኢሳይያስ 53፥1-2 ይመ.)

ተጨነቀ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ግፍ አደረጉበት››

አፉን አልከፈቱም

‹‹አፍ›› ሰው የሚናገረውን ይወክላል፡፡ አፍን መክፈት መናገር ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አልተቃወመም››

ለዕርድ እንደሚነዳ ጠቦት፣ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ

ሰዎች ሲጐዱትና ሲያዋርዱት ዝም ማለቱን አጽንዖት ለመስጠት ኢሳይያስ የያህዌን ባርያ ከጠቦትና ከበግ ጋር ያመሳስለዋል፡፡

ለዕርድ እንደሚነዳ በግ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰው ሲያርደው ዝም እንደሚል ጠቦት››