am_tn/isa/53/01.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እዚህ ላይ ኢሳይያስ ወደ ፊት የሚሆኑ ነገሮችን ባለፈው ጊዜ እንደ ተፈጸሙ አድርጐ ይናገራል፡፡ ይህ በእርግጥ እንደሚሆን አጽንዖት ይሰጣል፡፡

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ስለ ያህዌ ባርያ መናገር ቀጥሏል፡፡

ከእኛ የሰሙትን ያመነ ማን ነው?

ኢሳይያስ የተረዳው በጣም አስገራሚ በመሆኑ ምርኮኞቹ ያምኑ እንደሆነ ይጠይቃል፡፡ ‹‹እኛ›› የሚለው እርሱንና በምርኮ ያሉትን ይጨምራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኛ የሰማነውን ማመን በጣም ከባድ ነው››

የያህዌስ ክንድ ለማን ተገለጠ?

ክንድ የእግዚአብሔርን ኀይል ያመለክታል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ኀይሉን ለሕዝቡ ገለጠ››

እርሱ በያህዌ ፊት እንደ ቡቃያ አደገ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እርሱ›› ኢሳይያስ ከቡቃያ ጋር የሚያመሳስለው የእግዚአብሔርን ባርያ ያመለክታል፡፡ ይህም እንደ ደካማ መገለጡ ያመለክታል፡፡

ከደረቅም መሬት

‹‹ደረቅ መሬት›› ተክል የማያድግበት ጠንካራ መሬት ሲሆን፣ የያህዌ ባርያ የሚመጣበትን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፍጹም ከማይታሰብ ሁኔታ››