am_tn/isa/51/23.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

በአስጨነቁሽ እጅ አደርገዋለሁ

በቁጣው የሞላውን ዋንጫ እንዲጠጡ ያስገደዳቸው ያህል ያህዌ ጠላቶቻቸውን እንደሚቀጣ ይናገራል፡፡

በአስጨነቁሽ እጅ አደርገዋለሁ

ዋንጫው እጃቸው ላይ እንዲሆን በማድረግ ዋንጫው ውስጥ ካለው እንዲጠጡ ያህዌ ያስገድዳቸዋል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶችህን ከቁጣዬ ጽዋ ወይን ጠጅ እንዲጠጡ አስገድዳለሁ››

አስጨናቂዎችሽ

አስጨናቂዎች የሚለውን ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንቺን ያስጨነቁ›› ወይም፣ ‹‹መከራ ያደረሱብሽ››

እንድንራመድበት ጀርባሽን እንደ መሬት፣ እንደ መንገድ አድርጊልን

ጠላቶቻቸው በጀርባቸው መረማመዳቸውን መንገድ ላይ ከመራመድ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶችሽ በጀርባሽ እንዲረማመዱ መንገድ ላይ ተጋደሚ››