am_tn/isa/51/21.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

አንቺ የተጐዳሽ፣ የሰከርሽ

ያህዌ፣ ‹‹አንቺ›› የሚለው የተጐዳውን ሕዝብ ለማመልከት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናንት የተጐዳችሁና የሰከራችሁ ሕዝብ››

ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ

ከያህዌ ቁጣ ዋንጫ እንዲጠጡ በመገደድ እንደ ሰከሩ ሁሉ፣ ከመከራቸው ብዛት የተነሣ እንደ ሰካራም ስለሆኑ ሰዎች ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የያህዌን ቁጣ ዋንጫ ጠጥታችሁ የሰከራችሁ›› ወይም፣ ‹‹በደረሰባችሁ ከባድ መከራ እንደ ሰካራም የሆናችሁ››

እነሆ፣ የሚያንገደግደውን ዋንጫ፣ የቁጣዬ ዋንጫ የሆነውን ጽዋ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ከእንግዲህ

ቁጣው ከእነርሱ ያራቀው ዋንጫ ይመስል፣ ከእንዲህ ያህዌ በሕዝቡ እንደማይቆጣ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ በአንቺ ላይ አልቆጣም፤ ያንገዳገደሽን ጽዋ፣ ቁጣዬ የሞላበትን ዋንጫ ከአንቺ ወስጃለሁ››

እነሆ

ይህ ጥቅም ላይ የዋለው ቀጥሎ ለሚናገረው የአድማጮችን ትኩረት ለመሳብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አድምጡ››

የሚያንገደግድ ዋንጫ

‹‹ዋንጫ›› የሚለው ዋንጫው ውስጥ ያለውን ለማመልከት ነው፡፡ ኢሳይያስ 51፥17 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝብን የሚያንገደግድ የወይን ጠጅ ዋንጫ››

የቁጣዬ ዋንጫ የሆነው ጽዋ

ያህዌ በቁጣው ከተሞላው ጽዋ እንዲጠጡ ያስገደደ ያህል ሕዝቡን እንደቀጣ ይናገራል፡፡ ኢሳይያስ 51፥17 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቁጣዬ የተሞላ ጽዋ›› ወይም፣ ‹‹ቁጣዬ የሞላበት ዋንጫ››