am_tn/isa/51/19.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

የሚያዝንልሽ ማነው? የሚያጽናናሽ ማነው?

ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው የሚያዝንላቸው ወይም የሚያጽናናቸው አለመኖሩን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ጥያቄዎቹን ዐረፍተ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚያዝልሽ የለም… የሚያጽናናሽ የለም››

እነዚህ ሁለት መዓቶች

ሁለቱ ‹‹መዓቶች›› የተባሉት፣ ‹‹መፈራረስና ጥፋት››፣ ‹‹ራብና ሰይፍ›› ናቸው፡፡

መፈራረስና ጥፋት

እነዚህ ሁለት ቃሎች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፤ የጠላት ሰራዊት ምድሪቱን እንደሚያጠፋ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቻችሁ ምድራችሁን ባዶና ጠፍ አድርገዋል››

ራብና ሰይፍ

‹‹ራብ›› እና፣ ‹‹ሰይፍ›› በሕዝቡ ላይ የሚመጣውን መዓት ያመለክታሉ፡፡ ‹‹ሰይፍ›› ጦርነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ብዙዎቻችሁ›› በራብና በጦርነት ትሞታላችሁ››

በየጐዳናው ጥግ ተጋድመዋል

ይህ አጠቃላይ አነጋገር ነው፡፡ ብዙዎች በየጐዳናው ጥግ ይጋደማሉ ሲባል ሁሉም ማለት አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መንገዱ ላይ ይጋደማሉ››

በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዷቋ

ይህ የሚያመለክተው በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዷቋ ሕፃናት በጣም መድከማቸውንና ዐቅመ ቢስ መሆናቸውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዷቋ ዐቅመ ቢስ ሆነዋል›› ወይም፣ ‹‹ወጥመድ እንደ ያዘው ሚዷቋ ዐቅመ ቢስ››

ሚዷቋ

ይህ አጋዘን የሚመስል፣ ቀንድ ያለውና በፍጥነት የሚሮጥ እንስሳ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አጋዘን››

በያህዌ ቁጣ በአምላካችሁ ተግሣጽ ተሞልተዋል፡፡

የያህዌ፣ ‹‹ቁጣ›› እነርሱን ስለ ተቆጣ ያህዌ ሕዝቡን መቅጣቱን ያመለክታል፡፡ ይህ የሚያመለክተው በያህዌ ቁጣ የተሞሉ ያህል ሕዝቡ ክፉኛ መቀጣታቸውን ነው፡፡ ‹‹ተግሣጽ›› የሚለውን ቃል ግሥ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ ስለ ተቆጣቸውና ስለ ገሠጻቸው ያህዌ ክፉኛ ቀጣቸው››