am_tn/isa/51/17.md

2.3 KiB

ተነሺ ተነሺ ኢየሩሳሌም ሆይ ቁሚ

ኢየሩሳሌም እዚያ የሚኖረውን ሕዝብ ትወክላለች፡፡ ያህዌ የኢየሩሳሌም ሕዝብ እዚያ ሆነው እንደሚሰሙ አድርጐ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተነሡ፣ ተነሡ፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ንቁ››

ተነሺ፣ ተነሺ፣ ቁሚ

‹‹ንቂ፣ ተነሺ›› ተነሺ የሚለው ቃል መደገሙ የእስራኤል ሕዝብ እንዲነሣ የቀረበው ጥሪ አስቸኳይ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ቃል በቃል እነርሱን ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ ጥሪ አይደለም፡፡

ከያህዌ እጅ የጠጣሽ… የሚያንገደግደውን ዋንጫ ጭላጭ የጨለጥሽ፡፡

ያህዌ ሕዝቡን መቅጣቱ፤ በቁጣው ከሞላውን ዋንጫ ለመጠጣት መገደድ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ከቁጣው ዋንጫ ከጠጡ በኃላ ብዙ ወይን ጠጅ ጠጥቶ እንደ ሰከረ ሰው ይንገዳገዳሉ፡፡

ዝቃጭ

ዝቃጭ የሚባለው ፈሳሽ ሥር የሚቀር ጠጣሩ ነገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር››

ከያህዌ እጅ

ዋንጫውን ለሕዝቡ የሚሰጠው እርሱ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት እዚህ ላይ የያህዌ እጅ የሚያመለክተው ያህዌ ራሱን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እርሱ የሰጣችሁን››

ከሚያንገዳግድ ዋንጫ

‹‹በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው እንድትንገዳገዱ ከሚያደርግ ዋንጫ››

መንገዳገድ

ቀጥ ብሎ አለመሄድ፣ ሲራመዱ መሰናከል

የመራት አልነበረም… እጇን ይዞ የወሰዳት… አልነበረም

ሁለቱ ሐረጐች ተመሳሳይ ነገር ማለት በመሆናቸው መዋሐድ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚያመለክተው ከተማዋ እንደ ሰከረች፣ እጇንም ይዞ የሚመራ እንደሌላት ሴት ኢየሩሳሌምም ዐቅመ ቢስ መሆንዋን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሚረዳሽ የለም! እጇን ይዞ የሚመራት ልጅ እንደሌላት ሰካራም ሴት ነሽ››