am_tn/isa/51/16.md

1.6 KiB

ቃሌን በአፍህ አኖርሁ

ይህ የሚናገረው ቃሉ አንዳች ቁሳዊ ነገር ይመስል፣ ኢሳይያስ አፍ ውስጥ በማኖር ያህዌ ለኢሳይያስ ምን ማለት እንዳለበት የነገረው መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምን እንደምትል ነግሬሃለሁ››

በእጄ ጥላ ጋረድሁህ

የያህዌ፣ ‹‹እጅ›› ኀይሉን ያመለክታል፡፡ እርሱን ለመጠበቅ እጁ የሸፈነው ይመስል ያህዌ ኢሳይያስን እንደሚጠብቀው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ኀይሌ ጠብቆሃል›› ወይም፣ ‹‹ጋረድሁህ፤ በሰላምም ጠበቅሁህ››

ሰማያትን የተከልሁ

‹‹መትከል›› አንድን ነገር መሬት ውስጥ ማኖር ማለት ነው፡፡ እዚህ ያህዌ ሰማያትን ማጽናቱ፣ ሰማያት እርሱ የሚዘረጋው ድንኳን እንደሆኑና በካስማ አጥብቆ የተከላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰማያትን አጸናሁ››

ምድርን መሠረትሁ

በተለምዶ፣ ‹‹መሠረት›› ማለት ሕንፃውን ደግፎ የሚይዝ ከበታቹ ያለ የድንጋይ ሥራ ነው፡፡ እዚህም ላይ ምድርን በቦታዋ የሚይዝ ተመሳሳይ ዐይነት ነገር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ኢሳይያስ 24፥18 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡