am_tn/isa/51/14.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ዐንገታቸውን የደፉ

ይህ የሚያመለክተው የባቢሎናውያን ባርያዎች የነበሩትን እስራኤላውያን ነው፡፡ ይህ ሐረግ እንዴት ይሠሩ እንደ ነበር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባርያዎቹ››

ጥልቁ

ይህ የሚያመለክተው ሲኦልን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የሲኦል ጥልቅ›› ወይም ‹‹መቃብር››

እንጀራም አይጐድልበትም

‹‹እንጀራ›› ጠቅላላ ምግብን ይወክላል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምግብ አያጣም››

ባሕሩን የማማሰል

ይህ የሚያመለክተው አንድ ትልቅ ጐድጓዳ ሳህን ውስጥ ያለውን በማማሰያ እንደማማሰል ያህዌ ማዕበሉን ወደ ፊትና ወደ ኃላ፣ ወደ ላይና ወደ ታች የሚያደርገው መሆኑን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ባሕሩን የሚያማስለው›› ወይም፣ ‹‹ባሕሩን ወደ ላይ ወደ ታች የሚያደርገው››

ማዕበሉ እንዲያጓራ

ማጓራት ድብን ወይም አንበሳን ከመሳሰሉ በሕይወት ካሉ ነገሮች የሚወጣ ኀይለኛ፣ ጯኺ ድምፅ ነው፡፡ እዚህ ላይ ማዕበሉ ተመሳሳይ ድምፅ እንደሚያወጣ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ማዕበሉ በጩኸት ይላተማል››

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡