am_tn/isa/51/13.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ያህዌን ለምን ረሳህ… ምድርን?

ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው እርሱን መርሳት እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን ዐረፍተ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌን መርሳት አልነበረብህም… ምድር››

የፈጠረህን

ኢሳይያስ 17፥7 ላይ ይህን የያህዌን ስም እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ሰማያትን የዘረጋውን

‹‹ሰማያትን መዘርጋት›› አንድ ሰው ትልቅ ልብስ በሚዘረጋበት ሁኔታ እርሱም ሰማያትን የዘረጋ ይመስል ያህዌ ሰማያትን እንደ ፈጠረ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰማያትን እንደ ልብስ የዘረጋውን››

የምድር መሠረቶች

በተለምዶ መሠረት ከታች ሆኖ ሕንፃውን የሚደግፍ የድንጋይ ሥራ ነው፡፡ እዚህም ላይ ምድርን በቦታዋ የያዘና የቆመ መሠረት ነው ተብሎ ይታሰብ እንደ ነበር ያመለክታል፡፡ ኢሳይያስ 24፥18 ላይ ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ለማጥፋት የወሰነ የጨቋኙ

‹‹ለማጥፋት የተዘጋጀ፤ የጨቋኙ ጽኑ ቁጣ››

ጽኑ ቁጣ

‹‹ጽኑ›› ማለት ‹‹ብርቱ›› ወይም ‹‹ታላቅ›› ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ታላቅ ቁጣ››

የጨቋኙ ቁጣ የት አለ?

ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው ሕዝቡ ጨቋኞችን መፍራት እንደሌለባቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ጨቋኞቹ ይህን ያህል አስፈሪዎች አይደሉም፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጨቋኙ ቁጣ ያን ያህል አስፈሪ አይደለም››