am_tn/isa/51/11.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ከኢሳይያስ 38፥10 ጋር በጣም ይመሳሰላል፡፡

ያህዌ የተቤዣቸው

‹‹መቤዠት›› ማለት፣ ‹‹መታደግ›› ማለት ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው ያህዌ የታደጋቸውን ሰዎች ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የታደጋቸው››

ደስታ ለዘላለም ራሳቸው ላይ ይሆናል

የሰው ራስ የሰው ሁለንተና ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለዘላለም ደስ ይሰኛሉ››

ተድላና ደስታ… ሐዘንና ልቅሶ

እንደ፣ ‹‹ሐዘን›› እና ‹‹ልቅሶ›› ሁሉ፣ ‹‹ተድላ›› እና ‹‹ደስታ›› በመሠረቱ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በአንድነት ሲሆኑ እነዚህ ስሜቶች ምን ያህል ብርቱ እንደሆኑ አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡

ተድላና ደስታ ያጥለቀልቃቸዋል

ይህ የሚያመለክተው እንደ ብርቱ ወንዝ ተድላና ደስታ ሕዝቡን እንደሚያጥለቀልቁ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በተድላና በደስታ ይዋጣሉ›› ወይም፣ እጅግ ደስ ይላቸዋል ሐሤትም ያደርጋሉ››

ሐዘንና ልቅሶም ከእነርሱ ይሸሻሉ

እነዚህ ስሜቶች ሸሽተው የሚያመልጡ ይመስል ሕዝቡ ከእንግዲህ ሐዘንና ልቅሶ እንደማይገጥመው ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ አያዝኑም አያለቅሱም››