am_tn/isa/51/09.md

2.2 KiB

የያህዌ ክንድ ሆይ ተነሥ፣ ተነሥ ኀይልህንም ልበስ

የእርሱ ክንድ ሰው የሆነ ይመስል ሰዎች የያህዌ ክንድ በፍጥነት እንዲረዳቸው ይጠይቃሉ፡፡ ለክንድ መናገር ያልተለመደ ከሆነ በቀጥታ ለያህዌ እንዲናገር ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ ሆይ፣ ተነሥ፣ ተነሥ ኀይልህንም ልበስ››

የያህዌ ክንድ ሆይ… ተነሥ

እየረዳቸው ስላልነበረ ሰዎች የያህዌ ክንድ ከእንቅልፍ እንዲነሣ ይጠይቃሉ፡፡ ‹‹የያህዌ ክንድ›› ያህዌን በተለይም ሰዎችን መርዳቱን ይወክላል፡፡ ‹‹ተነሥ›› የሚለው ቃል የተደገመው ሰዎቹ ያህዌ ቶሎ እንዲረዳቸው አጥብቀው መፈለጋቸውን ለማሳየት ነው፡፡

ኀይልህንም ልበስ

ኀይል በጦርነት ጊዜ ብርታት እንዲሆናቸው የሚለበስ ልብስ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራስህን አበርታ››

ረዓብን የቆራረጥህ፣ ታላቁን ዘንዶ የወጋህ አንተ አይደለህምን?

ተናጋሪው የያህዌ ኀይል ታላቅ ነገር እንዲያደርግ አጽንዖት ለመስጠት በጥያቄዎች ይጠቀማል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተ ረዓብን የቆራረጥህ፣ ታላቁን ዘንዶ የወጋህ›› ረዓብ ባሕር ውስጥ የሚኖር እባብ ነው፡፡ ረዓብ የግብፅን መንግሥት ወይም ክፋትና ሁከት ይወክላል፡፡

የዳኑት እንዲሻገሩ… ባሕሩን ያደረቅህ አንተ አይደለህምን?

የያህዌ ኀይል ታላቅ ነገር እንዲያደርግ አጽንዖት ለመስጠት ተናጋሪው እንደ ገና በጥያቄዎች ይጠቀማል፡፡ ይህ የሚያመለክተው እስራኤላውያን በዚያ ውስጥ ተሻግረው ከግብፃውያን ሰራዊት እንዲያመልጡ ያህዌ ቀይ ባሕርን መክፈሉን ነው፡፡