am_tn/isa/51/04.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ ይናገራል፡፡

ስሙኝ… አድምጡኝ

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ በአንድነት ሲሆኑ እንዲሰሙ የተሰጠውን ትእዛዝ ያጠናክራሉ፡፡

ፍርዴም ለሕዝቦች ብርሃን ይሆናል

ፍርድ የእግዚአብሔርን ሕግ ይወክላል፤ ብርሃን ደግሞ እውነት የሆነውን ማወቅን ይወክላል፡፡ ይህም ማለት ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ሕግ ያውቃሉ፤ ይታዘዛሉ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እውነት የሆነውን ለሕዝቦች አስተምራለሁ›› ወይም፣ ‹‹ሕዝቦች ሕጌን ያውቃሉ››

ጽድቄ ቀርቦአል

‹‹ቀርቦአል›› የሚለው ሐሳብ፣ ‹‹ደርሶአል›› ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጽድቅ ቀርቦአል ማለት በቅርቡ ጽድቁን ይገልጣል ማለት ነው፡፡ ይህንንም የሚያደርገው ተስፋውን በመፈጸምና ሰዎችን በማዳን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በቅርቡ ጽድቄን አሳያለሁ››

ማዳኔም እየወጣ ነው

የእርሱ ማዳን ወደ እነርሱ እየወጣ ያለ ነገር እንደሆነ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሕዝብን አድናለሁ››

ክንዴ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል

የእግዚአብሔር ክንድ ኀይሉን ይወክላል፤ ፍርዱ መግዛትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በኀይሌ ሕዝቦችን እገዛለሁ››

ደሴቶች

ይህ የሚያመለክተው ከባሕር ማዶ ሩቅ አገር ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በደሴቶች የሚኖሩ ሰዎች›› ወይም፣ ‹‹ከባሕሩ ማዶ ባለው ምድር የሚኖሩ ሰዎች››

ክንዴንም በተስፋ ይጠብቃሉ

የእግዚአብሔር ክንድ እርሱ የሚያደርገውን ይወክላል፡፡ እዚህ ላይ ሰዎችን ማዳኑን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንዳች ነገር እንዳደርግ በተስፋ ይጠብቃሉ›› ወይም፣ ‹‹እንዳድናቸው በተስፋ ይጠባበቃሉ››