am_tn/isa/51/03.md

1.8 KiB

ያህዌ ጽዮንን ያጽናናታል

ኢየሩሳሌም ተብላ የምትጠራው የጽዮን ከተማ እዚህ ላይ የጽዮንን ሕዝብ ትወክላለች፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያህዌ የጽዮንን ሕዝብ ያጽናናል››

የፈራረሱ ቦታዎቿን ያጽናናል

‹‹የፈራረሱ ቦታዎች›› በእነዚያ ጠፍ ቦታዎች የሚኖረውን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፈራረሱ ቦታዎቿ የሚኖረውን ሕዝብ ያጽናናል››

የፈራረሱ ቦታዎቿ… ምድረ በዳዎቿ… በረሓ መስኮቿ

‹‹እርሷ›› የሚለው ጽዮንን ያመላክታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ከተሞች በሴት ጾታ ያጠራሉ፡፡

የፈራረሱ ቦታዎች

የወደሙ ቦታዎች ማለት ነው

ምድ በዳዋን፣ በረሓ መስኮቿን እንደ ዔደን፣… እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል

እነዚህ ሐረጐች በእስራኤል ያሉ ባዶ ቦታዎችን እግዚአብሔር ውብ እንደሚያደርግ ይናገራሉ፡፡ ትንቢቶቹ ወደ ፊት የሚሆኑት ነገሮች ባለፈው ጊዜ እንደ ተደረጉ ተነግሯል፡፡ ይህ አጽንዖት የሚሰጠው በእርግጥ እንደሚፈጸም ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምድረ በዳውን በረሓ፣ መስኮቿን እንደ ዔደን… እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፡፡››

ተድላና ደስታ በውስጧ ይገኛል

ተድላና ደስታ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ እዚያ ይገኛል ማለት እዚያ ይሆናል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ተድላና ደስታ እንደ ገና በጽዮን ይሆናል››