am_tn/isa/51/02.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

አባታችሁ፣ አብርሃም

እግዚአብሔር የጥንት ዝርያዎቻቸው አባት እንደሆነ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጥንት አባታችሁ አብርሃም›› ወይም፣ ‹‹የዘር ግንዳችሁ አብርሃም››

የወለደቻችሁ ሣራ

የአብርሃም ሚስት ሣራ እነርሱን የወለደች እናት እንደሆነች እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የዘር ግንዳችሁ የሆነች የአብርሃም ሚስት ሣራ››

ብቻውን በነበረ ጊዜ

ይህ ማለት ምንም ልጅ ሳይኖረው ማለት ነው፡፡ ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ምንም ልጅ በሌለው ጊዜ››

አበዛሁት

የአብርሃም ዘሮች መብዛት የአብርሃም መብዛት እንደሆነ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዘሮቹን አበዛሁ›› ወይም፣ ‹‹ብዙ ዘሮች እንዲኖሩት አደረግሁ››