am_tn/isa/51/01.md

1.5 KiB

እኔን ስሙ

‹‹እኔን›› የሚለው ያህዌን ያመለክታል፡፡

ወደ ዐለቱ… የወጣችሁበትንም ጉድጓድ ተመልከቱ

አንድን ነገር መመልከት ስለዚያ ነገር ማሰብን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለ ዐለቱ.. ስለ ወጣችሁበት ጉድጓድ አስቡ››

ተቆርጣችሁ የወጣችሁበትን ዐለት፣ ተቆፍራችሁ የወጣችሁበትንም ጉድጓድ ተመልከቱ

እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ሕዝብ ሲናገር፣ ከድንጋይ የተሠራ ሕንፃ እንደሆኑና የጥንት አባቶቻቸውም እግዚአብሔር እነርሱን የቆረጠበት ዐለት ወይም ጉድጓድ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ ይህን ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የጥንት አባቶቻችሁ ተቆርጣችሁ እንደ ወጣችሁበት ዐለት፣ ተቆፍራችሁም እንደወጣችሁበት ጉድጓድ ናቸው››

ተቆርጣችሁ የወጣችሁበት ዓለት

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ቆርጬ ያወጣኃችሁ ዐለት››

መሮ

‹‹በመሮ መቁረጥ›› ወይም፣ ‹‹መቆፈር››

የተቆፈራችሁበት ጉድጓድ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ እናንተን የቆፈርሁበት ጉድጓድ››