am_tn/isa/50/10.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የያህዌ ባርያ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል

ከእናንተ መካከል ያህዌን የሚፈራ ማን ነው? ለባርያው ድምፅ የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን በሌለበት ድቅድቅ ጨለማ የሚመላለስ ማን ነው ከሆነ… በአምላኩ

የያህዌ ባርያ ጥያቄዎቹን ያቀረበው ከሚናገራቸው ጋር ለመተባበር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእናንተ መካከል ያህዌን የሚፈራ፣ ለባርያው ድምፅ የሚታዘዝ፣ ግን ብርሃን በሌለበት ድቅድቅ ጨለማ የሚመላለስ ሰው ካለ… በአምላኩ››

ለባርያው ድምፅ የሚታዘዝ

‹‹ድምፅ›› የሚወክለው የያህዌ ባርያ የሚናገረውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለባርያው የሚታዘዝ››

ብርሃን በሌለበት ድቅድቅ ጨለማ የሚመላለስ

መከራ ውስጥ ያሉና ዐቅመ ቢስ የሆኑ ሰዎች በጣም ጨለማ በሆነ ቦታ እንደሚመላለስ ሰው እንደሆኑ የያህዌ ባርያ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መከራ ውስጥ ያለ ዐቅመ ቢስ››

በያህዌ ስም ይታመን በአምላኩም ይደገፍ

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ‹‹ስም›› የሚያመለክተው ያህዌ ራሱን ነው፡፡ በእግዚአብሔር መታመን በእርሱ መደገፍ ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በአምላኩ በያህዌ ይታመን››