am_tn/isa/50/07.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የያህዌ ባርያ መናገር ቀጥሏል፡፡

ስለዚህ አልዋረድም

ምንም እንኳ በደል ቢፈጸምበትም ለያህዌ በመታዘዙ አይዋረድም፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህም አላፍርም››

ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌአለሁ

‹‹ፊቴን›› የሚለው የሚያመለክተው ባርያውን ነው፡፡ ባርያው ለያህዌ ለመታዘዝ መቁረጡ ፊቱን እንደ ባልጩት ድንጋይ ማድረግ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፍጹም ቆርጫለሁ››

እንደማላፍር አውቃለሁ

የያህዌ ባርያ የወደ ፊቱን በተስፋ ይመለከታል፤ በያህዌ ጥሪ ይተማመናል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላቶቼ እንዳፍር ማድረግ እንደማይችሉ አውቃለሁ››