am_tn/isa/48/19.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ስለ ወደ ፊቱ የእስራኤል ሁኔታ መናገር ቀጥሏል፡፡

ዘርህ እንደ አሸዋ፣ የማሕፀንህም ልጆች ስፍር እንደሌለው ትቢያ ይሆኑ ነበር

ሁለቱም ሕዝቡ መቁጠር ከሚችሉት በላይ ዘሮቻቸው ይበዙ እንደ ነበር ያመለክታሉ፡፡

የማሕፀንህም ልጆች

የእስራኤል ሕዝብ ዘሮች እንደሚወለዱ ልጆች እንደሚሆኑ ያህዌ ይናገራል፡፡

ስማቸው አይቆረጥም ወይም አይደመሰሰም ነበር

የእስራኤል ሕዝብ መጥፋት እንደ ልብስ ወይም እንደ ዛፍ ቅርንጫፍ መቆረጥ ወይም መደምሰስ እንደሚሆን ያህዌ ይናገራል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስማቸውን አልቆርጥም ወይም አልደመስስም ነበር››

ስማቸውን

‹‹ስም›› የሚለው ቃል የእስራኤልን ስም የሚያስጠሩ ዘሮችን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እነርሱ››

አይቆረጥም ወይም አይደመሰስም

በዚህ ዐውድ ሁለቱም አገላለጾች የሕዝቡን መጥፋት ነው የሚያመለክቱት፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አይጠፋም››