am_tn/isa/48/17.md

1.4 KiB

የተቤዠህ… አምላክህ

እዚህ ላይ፣ ‹‹የአንተ›› የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል፡፡

የተቤዠህ

ኢሳይያስ 41፥14 ላይ ይህን ቃል እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

የእስራኤል ቅዱስ

ኢሳይያስ 1፥4 ላይ ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምኸው ተመልከት፡፡

መሄድ በሚገባህ መንገድ የሚመራህ

እንዴት መኖር እንዳለባቸው ያህዌ ሕዝቡን ማስተማሩ እነርሱን በትክክለኛው መንገድ መምራት ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ

ያህዌ መሆን ስለ ነበረበት ግን ስላልሆነ ነገር ይናገራል፡፡

ሰላምህና ብልጽግናህ እንደ ወንዝ፣ መዳንህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር

እነዚህ ሁለት ሐረጐች የሚናገሩት ስለ ተመሳሳይ ጉዳይ ነው፡፡ በሁለቱም እነዚህ በረከቶች እንደ ውሃ የሚፈሰሱ ይመስል እስራኤል በረከትን እንደምትለማመድ ያህዌ ይናገራል፡፡

መዳንህም እንደ ባሕር ሞገድ

ግሡን ካለፈው ሐረግ መውሰድ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መዳንህ እንደ ባሕር ሞገድ በፈሰሰ ነበር››