am_tn/isa/48/14.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ከእናንተ መካከል እነዚህን ነገሮች ያስታወቀ ማን ነው?

ያህዌ ጥያቄውን ያነሣው ጣዖቶች እነዚህን ነገሮች እንዳልነገሯቸው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከጣዖቶቻችሁ አንዱም ይህን አልነገሯችሁም››

የያህዌ አጋር ባቢሎን ላይ ዓላማውን ይፈጽማል፤ ከለዳውያንም ላይ ፈቃዱን ያደርጋል

የያህዌ፣ ‹‹አጋር›› የተባለው ቂሮስ ነው፡፡ ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ቢሆኑም ጥቅም ላይ የዋሉት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

ዓላማው

‹‹የያህዌ ዓላማ››

እኔ፣ እኔ

‹‹እኔ›› የሚለው የተደገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ራሴ››