am_tn/isa/48/12.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

ያዕቆብና እስራኤል

ሁለቱም የሚያመለክቱት የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡

እኔ የመጀመሪያው፣ የመጨረሻውም ነኝ

ይህ ሐረግ ለያህዌ ዘላለማዊ ባሕርይ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ሁሉንም የጀመርሁ እኔ ነኝ፤ ሁሉንም የምጨርስ እኔ ነኝ›› ወይም 2) ‹‹እኔ ሁሌም የነበርሁ፣ ሁሌም የምኖር ነኝ›› ኢሳይያስ 46፥6 ላይ ተመሳሳዩን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

እጄ፣ ምድርን መሠረተ፤ ቀኝ እጄ ሰማያትን ዘረጋ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› የሚያመለክተው ያህዌን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የምድርን መሠረት አኖርሁ፤ ሰማያትንም ዘረጋሁ››

የምድር መሠረት

መሠረት ከሥር ሆኖ ሕንፃውን ደግፎ የሚይዝ የድንጋይ መዋቅር ነው፡፡ እዚህም ላይ በተመሳሳይ መልኩ ምድርን የሚይዝ መዋቅር እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ኢሳይያስ 24፥18 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ሰማያትን ዘረጋሁ

ያህዌ ሰማያትን መፍጠሩን አንዳች የሚዘረጋ ነገር መዘርጋት ማለት እንደሆነ አድርጐ ይናገራል፡፡ ኢሳይያስ 42፥5 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ስጠራቸው በአንድነት ይቆማሉ

ያህዌ ሲጠራቸው መቆም ለእርሱ ለመታዘዝ ዝግጁ መሆን ማለት ነው፡፡ ምድርና ሰማያት እንደሚሰሙትና እንደሚታዘዙት ያህዌ ይናገራል፡፡

ስጠራቸው

ይህም ማለት፣ 1) ‹‹ምድርና ሰማያትን ስጠራቸው›› ወይም 2) ‹‹በሰማይ ያሉ ከዋክብትን ስጠራቸው›› ማለት ሊሆን ይችላል፡፡