am_tn/isa/48/01.md

1.3 KiB

ይህን ስሙ

‹‹መልእክቴን ስሙ›› ያህዌ እየተናገረ ነው፡፡

የያዕቆብ ቤት

እዚህ ላይ፣ ‹‹ቤት›› የያዕቆብን ዘር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የያዕቆብ ዘሮች››

በእስራኤል ስም የተጠራችሁ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰው ሁሉ የእስራኤል ሕዝብ እያለ የሚጠራችሁ››

ከይሁዳ ፍሬ የመጣችሁ

ይህ ሐረግ አጽንዖት የሚሰጠው እነርሱ በአካል የይሁዳ ዘር መሆናቸውን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የይሁዳ ዘር ናችሁ››

በእስራኤል አምላክ የምትታመኑ

‹‹የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ››

ራሳቸውን ይጠራሉ

ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ራሳችሁን ትጠራላችሁ››

የተቀደሰች ከተማ

ይህ የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን ነው፡፡

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡