am_tn/isa/47/14.md

980 B

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

እንደ ተዋረደች ንግሥት ባቢሎን ላይ ስለሚደርሰው ውድቀት መናገሩን ያህዌ ቀጥሏል፡፡

እንደ ገለባ ይሆናሉ፤ እሳትም ያቃጥላቸዋል

አስማተኞችና መተተኞች እሳት በቀላሉ እንደሚያቃጥለው ገለባ እንደ ሆኑ ያህዌ ይናገራል፡፡ ይህም ማለት እሳት ገለባ እንደሚያቃጥል፣ ያህዌ በፍጥነት ያጠፋቸዋል ማለት ነው፤ ባቢሎንን ለማዳን ዐቅም የላቸውም፡፡

የነበልባሉ እጅ

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› ብርታትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የነበልባሉ ኀይል››

የሚሞቁት ፍም፤ ተቀምጠው የሚሞቁት እሳት አይኖርም

ይህ ሰዎች የሚሞቁት ሳይሆን፣ የሚያጠፋ እሳት መሆኑን ያህዌ ይናገራል፡፡