am_tn/isa/47/08.md

1.1 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

እንደ ተዋረደች ንግሥት ባቢሎን እንደምትወድቅ ያህዌ መናገር ቀጥሏል፡፡

እናንት ደስታ የምትወዱ

‹‹እናንት ቅምጥሎች›› ይህ የባቢሎንን ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ ያመለክታል፡፡

ተማምነሽ የምትቀመጪ

ይህ ሀብቷንና ክብሯን በፍጹም እንደማታጣ በማሰብ ባቢሎን የነበራትን አጉል በራስ መተማመን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁሉም ደህና እንደሆነ የምታስቢ››

መበለት አልሆንም… የወላድ መካን አልሆንም

ሌሎች መንግሥታት በፍጹም ድል እንደማያደርጓት ባቢሎን የነበራት እምነት መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካን አልሆንም በማለት የማሰብ ያህል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

መበለት አልሆንም

‹‹ባል የሌላት ሴት አልሆንም››

በአንድ ቀን ውስጥ

‹‹ድንገት በአንድ ጊዜ››