am_tn/isa/47/06.md

1.4 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ያህዌ የተዋረደች ልዕልት ስለሆነችው ስለ ባቢሎን ውድቀት መናገር ቀጥሏል፡፡

እኔ ተቆጥቼ ነበር

‹‹እኔ›› ያህዌን ያመለክታል፡፡

ርስቴን አርክሼው ነበር

የእስራኤል ሕዝብ የእርሱ የተለየ ርስት እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የእኔ የተለየ ርስት የሆነውን ሕዝቤን አርክሼ ነበር››

አሳልፌ በእጅሽ ሰጠኃቸው

እዚህ ላይ፣ ‹‹እጅ›› የባቢሎንን ኀይል ወይም ቁጥጥር ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በሥልጣንሽ ሥር አደረግኃቸው››

በዕድሜ በገፉት ላይ ከባድ ቀንበር ጫንሽባቸው፡፡

ባቢሎን በዕድሜ የገፉትን መጨቆንዋ እንደ እንስሳት አንገታቸው ላይ ቀንበር ማድረግ እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡

ለዘላለም ንግሥት እሆናለሁ

እርሷ ለዘላለም የምትገዛ ይመስል ብዙ መንግሥታትን እንደ ልዕልት እንደምትገዛ ትናገራለች፡፡

እነዚህን ነገሮች አላስተዋልሽም

እነዚህን ነገሮች ልብ ውስጥ እንደማኖር ያህዌ ስለ ነገሮች በጥንቃቄ ማሰብ እንደሚገባ ይናገራል፡፡