am_tn/isa/47/03.md

2.0 KiB

አያያዥ ዐረፍተ ነገር

ያህዌ የተዋረደች ንግሥት የሆነችው የባቢሎንን ውድቀት መናገር ቀጥሏል፡፡

ዕርቃንሽ ይገለጣል

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዕርቃንሽን ትሆኛለሽ››

ኀፍረትሽ ይታይ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ኀፍረት›› የሚለው የሰውን ድብቅ አካል ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰዎች ኀፍረትሽን ያያሉ›› ወይም፣ ‹‹ሰዎች ድብቅ አካልሽን ያያሉ››

የሚቤዠን

‹‹የእኛ›› የሚለው ኢሳይያስንና የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል፡፡ ኢሳይያስ 41፥14 ላይ ይህን እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥24 ላይ ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

የእስራኤል ቅዱስ

ኢሳይያስ 5፥16 ላይ ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

የከለዳውያን ሴት ልጅ

ይህ ሐረግ እንደ ሴት ልጅ የተመሰለችው የባቢሎንን ከተማ ያመለክታል፡፡ ከተማዋ፣ ‹‹በሴት ልጅ›› መመሰልዋ ከለዳውያን እርሷን በጣም መወደዳቸውን ያመለክታል፡፡ ኢሳይያስ 47፥1 ላይ ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡

ከእንግዲህ አትጠሪም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ሰዎች አንቺን አይጠሩሽም፡፡

የመንግሥታት ልዕልት

የባቢሎን መንግሥት ዋና ከተማ የሆነችው ባቢሎን ብዙ መንግሥታትን ትገዛ የነበረች ልዕልት እንደሆነች ያህዌ ይናገራል፡፡