am_tn/isa/47/01.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

በዚህ ምዕራፍ የተዋረደች ንግሥት ይመስል፣ ያህዌ ስለ ባቢሎን መውደቅ ይናገራል፡፡

ትቢያ ላይ ተቀመጪ፤ የባቢሎን ድንግል ልጅ ሆይ፣ መሬት ላይ ተቀመጪ…የከለዳውያን ልጅ ሆይ

እነዚህ ሁለት ሐረጐች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ትቢያ ላይ መቀመጥ የውርደት ምልክት ነው፡፡

የባቢሎን ድንግል ልጅ… የከለዳውያን ልጅ

ሁለቱም ሐረጐች የሚያመለክቱት እንደ ሴት ልጅ የተነገረላት የባቢሎንን ከተማ ነው፡፡ ከተማዋ፣ ‹‹ሴት ልጅ›› መሆንዋ ሕዝቡ ለእርሷ ያለውን ፍቅር ያመለክታል፡፡

ያለ ዙፋን

እዚህ ላይ፣ ‹‹ዙፋን›› የመግዛት ሥልጣንን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ያለ የመግዛት ሥልጣን››

ከእንግዲህ ውብ ወይም ለግላጋ ተብለሽ አትጠሪም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእንግዲህ ሰዎች ውብና ለግላጋ በማለት አይጠሩሽም››

ውብና ለግላጋ

እነዚህ ሁለት ቃሎች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፡፡ ያማረና በምቾት መኖርን ያመለክታሉ፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በጣም ያማርሽ›› ወይም፣ ‹‹በጣም የተመቸሽ››

ወፍጮ

እህል ለመፍጨት የሚያገለግል ትልቅ ድንጋይ