am_tn/isa/45/22.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ መናገር ቀጥሏል

ትድኑ ዘንድ ወደ እኔ ተመለሱ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም አድናችኃለሁ››

የምድር ዳርቻዎች ሁሉ

ሩቅ ቦታ የሚኖሩ ሰዎች የምድር ዳርቻዎች ላይ እንደሚኖሩ ተነግሯል፡፡ ይህ ማለት በዳርቻዎቹ መካከል ያለ ማንኛውም ቦታ ማለትም ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድር ሩቅ ቦታ ያላችሁ ሁሉ›› ወይም፣ ‹‹በምድር ሁሉ››

የምድር ዳርቻዎች ሁሉ

ይህ ሐረግ፣ ‹‹በምድር ዳርቻዎች ሁሉ›› የሚኖሩ ሰዎችን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በምድር ሩቅ ቦታ የምትኖሩ ሁሉ›› ወይም ‹‹በምድር ሁሉ የምትኖሩ››

ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንብረከካል፤ አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል

‹‹ጉልበት›› እና፣ ‹‹አንደበት›› የሚወክሉት ሰዎችን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰው ሁሉ በፊቴ ይንበረከካል፤ ማንኛውም ሰው በእኔ ይምላል››